News

የኢቦላ በሽታ ከመከሰቱ አስቀድሞ ለመከላከል የአሰልጣኞች ስልጠና ተሰጠ

61420183የኢቦላ በሽታ ለከባድ ህመም የሚዳርግና በኢቦላ ቫይረስ አማካኝነት የሚከሰት ተላላፊ በሽታ ነው፡፡ በሽታው በፍጥነት ከሰው ወደ ሰው የሚተላለፍ ሲሆን በበሽታው ከሚያዙት ውስጥ እስከ 90 በመቶ የሚደርሱት የህክምና እርዳታ ካልተደረገላቸው ለሞት ይዳረጋሉ፡፡ ሆኖም በበሽታው ከተያዙት መካከል ተጓዳኝ እርዳታ ከተደረገላቸው 52 ፐርሰንት የመዳን እድል ይኖራቸዋል፡፡ የኢቦላ በሽታ ከዚህ በፊት ክትባት ያልነበረው ቢሆንም በአሁኑ ወቅት በተወሰነ መልኩ በአገልግሎት ላይ እየዋለ ይገኛል፡፡ በሽታው ይህ ነው የሚባል ፍቱን ህክምና ያልተገኘለት ከመሆኑም በላይ በሽታው በአለማችን ካሉ አደገኛ ከሚባሉት በሽታዎች መከከል አንዱ ነው፡፡
በአሁኑ ወቅት በዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ የኢቦላ ወረርሽኝ በአዲስ መልክ የተከሰተ መሆኑ ይታወቀል፡፡ በሽታው ወደ ሌሎች አጎራባች አገራት እንዳይዛመት ለመቆጣጠርና ለማጥፋት የሃገሪቱ መንግስት፣የአለም ጤና ድርጅትን እና በርካታ አጋር ድርጅቶችን ጨምሮ ከፍተኛ ርብርብ በማድረግ ላይ ይገኛሉ፡፡ በመሆኑም በሽታው በአሁኑ ሰዓት ለአለም የሚያሰጋ ችግር ሆኖ በማይታይበት ደረጃ ላይ በማድረስ በቁጥጥር ስር እየዋለ ይገኛል፡፡ ሃገራችን ኢትዮጵያም ገና ከጅምሩ በዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ የኢቦላ ወረርሽኝ ሲከሰት የብሔራዊ የኢቦላ አስተባባሪ ኮሚቴ በማቋቋም የኢቦላ ወረርሽኝ ዝግጅትና ምላሽ አሰጣጥ ሀገራዊ እቅድ በማዘጋጀት ከፍተኛ የሆነ የቅድመ ዝግጅት ስራ እየተሰራ ይገኛል፡፡
ከቅድመ ዝግጅት እንቅስቃሴዎች መከከል አንዱ የጤና ባለሙያዎችን ስለ ኢባላ ያላቸውን እውቀት በተለይም በሽታውን ከመከላከል አንጻር፣በበሽታው የተያዙትን እንዴት መርዳት እንደሚቻልና ተላላፊነቱን ለመግታት የሚደረጉትን ጥንቃቄዎች ላይ የእውቀት ግንዛቤን በሚገባ ከፍ ለማድረግ የሚሰጡ ስልጠናዎች ተጠቃሽ ናቸው፡፡
በመሆኑም የኢትዮጵያ የሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት የሕብረተሰብ ጤና አደጋዎች ቁጥጥር ማእከል ለከፍተኛ የጤና ባለሙያዎች የአሰልጣኞች ስልጠና ከግንቦት 27 እስከ ሰኔ 2/2010 ዓ.ም በቢሾፍቱ ከተማ በሊሳክ ሪዞርት ኢቦላን አስመልክቶ ስልጠና ሰጥቷል፡፡
የስልጠናውም ዋና ዓላማ ኢቦላን ለመከላከል በሚደረገው ቅድመ ዝግጅት ከጤና ጥበቃ ሚኒስቴር፣ከኢትዮጵያ መድሃኒት ቁጥጥር ባለስልጣን፣ከአዲስ አበባ ጤና ቢሮ የተውጣጡ እና ኢቦላን ለመከላከል ዘምተው የተመለሱ ከፍተኛ ባለሙያዎችን በማካተት የአሰልጣኞች ስልጠና በመስጠት የክልል ባለሙያዎችን በስራቸው ያሉትን እንዲያሰለጥኑ ለማድረግ የተዘጋጀ ስልጠና ነው፡፡
ስልጠናው በኢንስቲትዩቱ ባለሙያዎች እና በአለም አቀፍ ጤና ድርጅት ባለሙያዎች የተሰጠ ሲሆን ስልጠናው በጥያቄና መልስ፣በፊት ለፊት ገለጻ ከመሰጠቱም በላይ ኢቦላ በኢትዮጵያ ቢከሰት ወይም ጥርጣሬ ቢፈጥር በችግሩ የተጠረጠሩ እና በሽታው የተገኘባቸውን ለማከምና ለማቆያ በተዘጋጀው በቦሌ ጨፌ ጤና ጣቢያ ባለሙያዎች ተገኝተው በተግባር ስልጠናውን ወስደዋል፡፡
በተግባሩ ስልጠና ወቅት ሰልጣኞች በሽታውን ለመከላከል የሚለበሰውን ልብስ ከመጀመሪያ አለባበስ እስከ ማውለቅ ደረጃ ያሉትን እንዲሁም በበሽታው የተያዘውን እና የተጠረጠረውን ግለሰብ በመርዳት ደረጃ የሚደረጉ ከፍተኛ ጥንቃቄዎችን ስለማድረግ በጥልቀት ለባለሙያዎቹ ተሰጥቷል፡፡
በመጨረሻም ከስልጠናው መጠናቀቅ በኋላ ስለማቆያው ቦታ ዝግጅት ላይ ውይይት የተደረገ ሲሆን ከሰልጣኞች በተለይም ኢቦላን ለማጥፋት ከዘመቱ ባለሙያዎችና ከአለም አቀፍ ጤና ድርጅት ባለሙያዎች መስተካከል ያለባቸውን ነገሮች ጥቆማና እጅግ ገንቢ የሆኑ አስተያየቶች የተሰጡ ሲሆን የኢንስቲትዩቱ የሕብረተሰብ ጤና አደጋዎች ቁጥጥር የአስቸኳይ ማስተባበሪያ ማእከል (EOC) አስተባባሪ (Incident manager) የሆኑት አቶ ዘውዱ አሰፋ የማጠቃለያ ንግግር ባደረጉበት ወቅት የተሰጡትን አስተያየቶች እና ጥቆማዎች በሚገባ በመቀበል መስተካከል ያለባቸውን ጉዳዮች በአፋጣኝ እንደሚስተካከሉ ከመናገራቸውም በላይ ስልጠናወን ለወሰዱ ባለሙያዎች በቀጣይ ስልጠናው ወደ ክልል በሚወርድበት ወቅት ትልቁን የማስተባባር ድርሻ መውሰድ እንዳለባቸው፣ በበሽታው የተጠረጠረ ቢገኝ በማንኛውም ጊዜ ምላሽ ለመስጠት የተዘጋጁ መሆን እንዳለባቸውና የማከሚያው ወይም የማቆያው ማእከል ደረጃውን የጠበቀ እንዲሆን እንዲሁም በክልሎች በሚቋቋምበት ጊዜ የድርሻቸውን መወጣት እንዳለባቸው አሳስበዋል፡፡
በአጠቃላይ እንደሃገር ይህንን አስከፊ በሽታ አስቀድሞ ለመከላከል እየተደረገ ያለው እንቅስቃሴ ከፍተኛ ሲሆን በቀጣይም ለክልል ሕብረተሰብ ጤና አደጋዎች ቁጥጥር ማእከል፣ለክልል መድሃኒት ቁጥጥር ባለስልጣን ባለሙያዎች እና ኢቦላ ላይ ለሚሰሩ ባለሙያዎች እንደሚሰጥ ለማወቅ ተችሏል፡፡

61420184  6142018461420186

Preparedness for EVD Protection Kicked Off

The Ethiopian Public Health Institute’s (EPHI) Public Health Emergency Management (PHEM) is taking the necessary preparedness measures to protect the Ebola Viral Disease (EVD) from occurring in the country.
On May 12, 2018 PHEM conducted EVD orientation following the declaration of EVD outbreak in Democratic Republic of Congo (DRC) by the country’s Ministry of Health on May 8, 2018 for the PHEM staffs and field epidemiology residents from Addis Ababa University (AAU) and St. Paul Hospital Millennium Medical College (SPHMMC) at EPHI’s Training Center.

e3

PHEM Activated It’s EOC

The Ethiopian Public Health Institute’s (EPHI) Center for Public Health Emergency Management (PHEM) activated its Emergency Operation Center (EOC) on May 16, 2018 for the 2nd time. It is to be recalled that EOC was established in July, 2017 and was activated in August 2017 for Acute Watery Diarrhea outbreak response.
Deputy Director General of EPHI Dr. Beyene Moges has briefed the participants the objectives of the activation of the EOC. During the meeting the Incident Manager, Mr. Zewdu Assefa has presented the global situation including Ebola outbreak in DRC, circulating cVDPV2 in Kenya and Somalia, and current situations in Ethiopia including diseases and natural emergencies such as flooding.

e2

PHEM Conducted 2nd Round Orientation on EVD Conducted

The Ethiopian Public Health Institute’s (EPHI) Center for Public Health Emergency Management (PHEM) conducted the 2nd round orientation about Ebola Viral Disease (EVD) on May 19, 2018 at EPHI Training Center for the staffs, FETP residents from AAU, SPHMMC, EPHI’s Public Relation staffs, National Laboratory Capacity Building Directorate and volunteers.

e1

 

ዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ ዳግም የተከሰተው ኢቦላ በተባለ ቫይረስ አማካኝነት የሚተላለፈውን የበሽታ ወረርሽኝ መነሻ በማድረግ ኢትዮጵያ በሽታውን አስቀድሞ ለመካላከልና ለመቆለመቆጣጠር የሚያስችሏትን የቅድመ ዝግጅት ስራዎች በተደራጀ መልኩ እየሰራች ትገኛለች፡፡

ኢቦላ በተባለ ቫይረስ አማካኝነት የሚተላለፈው የበሽታ ወረርሽኝ ዲሞክራቲክ ሪፑብሊክ ኮንጎ እንዲሁም በተወሰኑ የምዕራብ አፍሪካ አገራት በተለያዩ ጊዜያት በመከሰቱ የሰባዊ፣ የማሕበራዊና የምጣኔ ሃብት የከፉ ጉዳቶችን ማድረሱ የሚታዎስ ነው፡፡ እነዚህ የኢቦላ ወረርሽኞች በተከሰቱባቸው ጊዜያት ኢትዮጵያ የተለያዩ የቅድመ መከላከል ሥራዎችን በመስራት ወረርሽኙ ወደ ሀገራችን እንዳይገባ ከፍተኛ ርብርብ ስታደርግ ቆይታለች፤ ከነዚህ ዝግጅቶች በተጨማሪም ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው የጤና ባለሙያዎችን የበሽታው ወረርሽኝ ወደተከሰተባቸው የምዕራብ አፍሪካ ሀገራት በመላክ በሽታዉ በቁጥጥር ስር እንዲዉል የበኩሏን አስተዋጽኦ አበርክታለች፡፡ በአሁኑ ወቅት ደግሞ ይህ ወረርሽኝ በዲሞክራቲክ ሪፑብሊክ ኮንጎ ቢኮሮ በምትባል የኢኩየተር ክልል የምትገኝ መንደር ከሚያዚያ 30, 2010 ዓ.ም. ጀምሮ በአዲስ መልክ የተከሰተ መሆኑን የዓለም ጤና ድርጅት (WHO) እና የዲ.ሪ.ኮንጎ መንግስት አረጋግጠዋል፡፡
በዚህም መሠረት ደቡብ ሱዳን የዲሞክራቲክ ሪፑብሊክ ኮንጎ እና ኢትዮጵያ የጋራ አዋሳኝ ሀገር በመሆኗ እና በየብስ ትራነስፖርት የሰዎች እንቅስቃሴ ሊኖር በመቻሉ እንዲሁም ከኡጋንዳ እና ዲ.ሪ.ኮ ጋር ደግሞ የቀጥታ የአየር ትራንስፖርት ግንኙነት ያለን በመሆኑ እና በሽታው ድንበር ዘለልና በከፍተኛ ደረጃ በወረርሽን መልክ የሚዛመት ስለሆነ አገራችን ቀደም ሲል የነበራትን ልምድ ተጠቅማ በከፍተኛ የፖለቲካ አመራሩ የሚመራና ሁሉንም ባለድርሻ አካላት ያካተት ከፍተኛ ግብረ ኃይል በብሔራዊ ደረጃ የተደራጀ ሲሆን ይህ ግብረ ኃይልም በተመሳሳይ አደረጃጀት በሁሉም ክልሎች እና ከተማ አስተዳደሮች ላይ ተዋቅሮ የኢቦላ ቫይረስ ወረርሽኝ መከላከል የዝግጁነት ስራው እየተሰራ ይገኛል፡፡
ከነዚህም የኢቦላ ቫይረስ መከላከል የዝግጅነት ሥራዎች መካከል፡-
   •ሁሉም ክልሎች እና ከተማ አስተዳደሮች በየደረጃው እንዲያውቁት እና አስፈላጊውን የቅድመዝግጅት ስራ እንዲሠሩ የማንቂ ደብዳቤ ተልኳል፡፡
   •ከፌደራል እስከ ወረዳ ባሉ በሁሉም የአስተዳደር መዋቅሮች የኢቦላ መከላከል ቅድመ ዝግጅት አስተባባሪ ግብረኃይል እንዲቋቋም ተደርጓል፤
   •የኢ.ፌ.ዲ.ሪ ጤና ጥበቃ ሚኒስትም በሽታው ሊከሰትባቸው ይችላሉ ተብለው የሚገመቱትን ቦታዎች በመለየት የበሽታው የቅኝት ስርዓት በማጠናከር አስፈላጊውን ቅድመ ዝግጅት በማድረግ በኢንተርናሽናል ኤርፖርቶችና በዋና ዋና የድንበር በሮች ላይ ጠንካራ የቁጥጥር ስርዓት ዘርግቷል፤
   •ከዚህ በፊት በምዕራብ አፍሪካ ተከስቶ በነበረው የኢቦላ ወረርሽኝ ወቅት ድጋፍ ለማድረግ ተሰማርተው የነበሩ እና በሀገር ውስጥ በቅድመ ዝግጅት ስራው ላይ ከፍተኛ ተሳትፎ ያደረጉ ባለሙዎችን ስም ዝርዝር በመያዝ በዝግጁነት ስራው ላይ እንዲሳተፍ ተደርጓል፡፡
   •በሁለቱም ዓለም አቀፍ የበረራ ጣቢያዎች (ድሬዳዋ እና ቦሌ) የሚገቡ ከዲሞክራቲክ ሪፑብሊክ ኮንጎ እና አካባቢ አገራት እንዲሁም ወደ እነዚህ ሀገራት በቅርብ ተጉዘው የሚያውቁ የአየር መንገዱ ደንበኞች ላይ ለበሽታው መጋለጣቸውን የሰውነት ሙቀት በመለካት /thermoscaning/ የልየታ ምርመራ ማድረግ ተጀምሯል፤
   •ለበሽታው የተጠረጠሩ የአየር መንገዱ ተጓዦች የሚቆዩበት ማዕከል /quarantine center/ በአየር መንገዶቹ ውስጥ ተደራጅቷል፡፡
   •በሽታው ቢከሰት አስፈላጊውን ህክምና እንዲሰጡ የተመረጡ ጤና ተቋማት በሰው ኃይልና በግብዓት እንዲደራጁ ተደርጓል፡፡
ይህንንም የመከላከል ስራ ውጤታማ ለማድረግና የበሽታው ወረርሽኝ በሀገራችን እንዳይከሰት የሁሉም ህብረተሰብ ክፍልና ባለድርሻ አካላት ጠንካራ ተሳትፎ እጅግ አስፈላጊ መሆኑን የጤና ጥበቃ ሚኒስቴር በፅኑ ያምናል፡፡
በመሆኑም፡-
   1.ወደ ዲ.ሪፐብሊክ ኮንጎ እና አካባቢው ለሚሄዱና ለመሄድ እቅድ ላላቸው ዜጎች መረጃውን በማድረስ፣
   2.ከእነዚህ አካባቢዎች በማንያውም የመጓጓዣ ዘዴ ወደ ኢትዮጵያ የሚገቡ ዜጎች ከቤተሰባቸው ጋር ከመቀላቀላቸው በፊት አስፈላጊውን ምርመራ በአየር መንገድ ወይም በድንበር አካባቢ በተቋቋሙት የልየታ ጣቢያዎች እንዲመረመሩ መረጃ በመስጠት ወይም ሪፖርት በማድረግ፤
   3.በጎረቤት፣ በቤተሰብ አባላት፣ በስራ፣ በእምነት እና በልዩ ልዩ ተቋማትና ስፍራዎች የበሽታው ምልክት የታየባቸውን ሰዎች በአፋጣኝ ወደ ጤና ተቋማት ሪፖርት በማድረግና በ952 ወይም 8335 የነፃ የስልክ መስመሮች በመደወል መረጃ በመስጠት የበኩላቸውን ድርሻ እንዲወጡ ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ማሳሰብ ያስፈልጋ፡፡

የኢቦላ ቫይረስ በሽታ ወረርሽኝን በጋራ እንከላከል!!
ፌደራል ጤና ጥበቃ ሚኒስቴር
ግንቦት 7, 2010 ዓ.ም.
አዲስ አበባ

የኢቦላ ቫይረስ በሽታ ወረርሽኝ ለመከላከል የሚረዱ መሰረታዊ መረጃዎች

ኢቦላ በሽታ ምንድን ነው?
   •ኢቦላ በሽታ ኢቦላ ቫይረስ በሚባል ተህዋሲያን አማካኝነት የሚመጣ ገዳይ በሽታ ነው፤
   •በሽታው ብዙን ጊዜ በከፍተኛ ትኩሳትና በተለያዩ የሰውነት ቀዳዳዎች የመድማት ሁኔታዎች ያስከትላል፤
   •የኢቦላ ቫይረስ በከፍተኛ ሁኔታ ተዛማች ቢሆንም መከላከል ግን ይቻላል፣
   •የኢቦላ በሽታ ከያዘን በአጭር ጊዜ ለገድል የሚችል በሽታ ነው፡፡


የኢቦላ በሽታ ምልክቶች ምን ምን ናቸው
   •ትኩሳት፣
   •ትውከት፣
   •ተቅማጥ፣
   •የሆድ ህመም፣
   •ራስ ምታት፣
   •ኩፍኝ የሚመስል የቆዳ ሽፍታ፣
   •በተለያዩ የሰውነት ቀዳዳዎች መድማት (ሊኖርም ላይኖርም ይችላል)
   •የአይን መቅላት የመሳሰሉት ናቸው


ኢቦላን እንዴት መከላከል ይቻላል?
   •የበሽታው ምልክት የታየባቸውን ግለሰቦች ቶሎ ወደ ህክምና ቦታ በመውሰድ እርዳታ እንዲያገኙ ማድረግ ወይም ለጤና ተቋማት ማሳወቅ፣
   •ለኢቦላ በሽታ ተጋላጭ የሆነ ሰውን ገላ ከነካን ወዲያውኑ እጅን በውሃና ሳሙና በሚገባ መታጠብ፣
   •በኢቦላ በሽታ ምክንያት የሞተ ሰውን አስከሬን አለመንካትና በባለሙያ በሚገባ በአስከሬን መጠቅለያ እንዲሸፈን ማድረግ እና ወዲያውኑ በባለሙያ መቅበር፣
   •ከቀብር መልስ እጅን በጋራ የመጣጠቢያ ስፍራ አለመታጠብ፣
   •በበሽታው ከተያዘ ሰው የሰውነት ፈሳሽ ጋር ንክኪ አለመፍጠር፣
   •በበሽታው የተያዘ ሰው ለመርዳት እንደ ጓንት፣ የአይን መነፅር፣ የአፍና አፍንጫ ሽፋንና የመሳሰሉትን የመከላከያ መሳሪያዎችን መጠቀም/ በመልበስ፣
   •ለተሟላ ጥንቃቄ እና እንክብካቤ ታማሚውን ወደ ሕክምና ተቋም በአፋጣኝ መወሰድ
   •ከታማሚው ሰው ጋር ንክኪ ያላቸውን አልባሳት፣ እቃዎችና እና ምንጣፎችን በክሎሪን ዘፍዝፎ ከዚያ ማጽዳት፣


ኢቦላ በሽታ እንዴት ይተላለፋል?
   •ኢቦላ እንደ ደም፣ ምራቅ፣ አይነ ምድር፣ ትውኪያ፣ ሽንት፣ ላብና ከመሳሰሉት በበሽታው ከተያዘ ሰው የሰውነት ፈሳሽ ጋር ቀጥተኛ ንክኪ በማድረግ፣
   •ታማሚው የተጠቀመባቸውና በሰውነት ፈሳሽ የረጠበ አንሶላና የአልጋ ልብስ የመሳሰሉ ጋር ንክኪ ሲኖር፣
   •በበሽታው የቴዘ ሰው የሰውነት ፈሳሽ በጤነኛ ሰው አይን ውስጥ ሲረጭ፣
   •በበሽታው የተያዘ ሰው የተጠቀመባቸው ሹልና ስለታም ነገሮችን ስንጠቀም፣
   •በኢቦላ በሽታ የሞተ ሰው አስከሬን ጋር መነካካት፣
   •በዚህ በሽታ የሞቱ እንደ ዝንጆሮ፣ የሌሊት ወፍ የመሳሰሉትን መንካት በመሳሰሉት ይተላለፋል፡፡


እናስታውስ!!
   •ኢቦላ መከላከል የምንችለው ነገር ግን በአጭር ጊዜ የሚገድል በሽታ ነው፤
   •ኢቦላ በቀላሉ ከሰው ወደ ሰው መተላለፍ የሚችል በሽታ ነው፤
   •በበሽታው ከተያዘ ሰው የሰውንት ፈሳሽ ጋር ንክኪ ማድረግ ለበሽታው አጋላጭ ባህሪ መሆኑን አይዘንጉ!!
   •ዘወትር እጅን በሳሙናና በውሃ በደንብ በመታጠብ ኢቦላ በሽታን መከላከል ይቻላል፡፡
   •በኢቦላ በሽታ የተጠረጠረ ስው ሲያጋጥም በአቅራቢያዎ ላለ ጤና ተቋም ሪፖርት ያድርጉ፡፡
   •በኢቦላ በሽታ ህይወቱ ያለፈ ሰው አስከሬን በአፋታኝ በባለሙያ በመታገዝ እንዲቀበር ያድርጉ
   •በኢቦላ በሽታ የተያዘን ስው በአፋጣኝ ወደ ህክምና ተቋም በመውሰድ የህክምና እርዳታ እንዲያገኝ በማድረግ ሊፈጠር የሚችለውን የበሽታው መዛመትና ሊደርስ የሚችለውን የሞት አደጋ እንከላከል፡፡