contact us

Who's Online

We have 74 guests and no members online

anti tewasiyana bየኢንስቲትዩቱ የባክትሮሎጂ ፓራሳይቶሎጂ እና እንሰሳት ነክ በሽታዎች ምርምር ዳይሬክቶሬት የጸረ ተህዋስያን ብግርነት የዳሰሳ ጥናት ዓመታዊ የምክክር ስብሰባ ከታህሳስ 23 እስከ 24/2013 ዓ.ም በቢሾፍቱ ከተማ ተካሄደ፡፡
የጸረ ተህዋስያን ብግርነት የዳሰሳ ጥናት ፕሮግራም በሃገር ደረጃ እ.ኢ.አ በ2017 በ4 የቅኝት የዳሰሳ ጥናት የጤና ተቋማት የተጀመረ ሲሆን በአሁኑ ሰዓት 9 የቅኝት የዳሰሳ ጥናት ተቋማት በመድረስ በዘንድሮው ዓመት 3ኛውን ዙር ዓመታዊ የምክክር ስብሰባ በማካሄድ አጠናቋል፡፡
ዶ/ር ጌታቸው ቶሌራ የኢንስቲትቱ ም/ዋና ዳይሬክተር የምክክር ስብሰባ የመክፈቻ ስነ-ስርዓት ወቅት የጸረ ተህዋስያን መድሃኒት ብግርነት በአሁኑ ሰዓት በዓለም ደረጃ ከፍተኛ የጤና ችግር መሆኑን፣የአለም ጤና ደርጅት የወቅቱ የጤና ችግር ብሎ ካስቀመጣቸው 10 ትኩረት ከተደረገባቸው ውስጥ የጸረ ተህዋስያን መድሃኒት ብግርነት አንዱ መሆኑን፣ በዚህም መሰረት ሃገራችን ችግሩን ለመቅረፍ ትልቅ ትኩረት ሰጥታ ከተለያዩ መንግስታዊና መንግስታዊ ካልሆኑ ተቋማት ጋር በቅንጅት እየሰራች የምትገኝ መሆኑን ጠቅሰው ከምክክር ስብሰባው የሚገኙ የተለያዩ ሃሳቦችና አቅጣጫዎች በመጠቀም በቀጣይ በርካታ ስራዎች የሚሰሩ መሆናቸውን ሰፊ ማብራሪያ ሰጥተዋል፡፡
ዶ/ር ገረመው ጣሰው የኢንስቲትዩቱ የባክትሮሎጂ ፓራሳይቶሎጂ እና እንሰሳት ነክ በሽታዎች ምርምር ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተርና የተለያዩ የአጋር ድርጅት ተወካዮች የጸረ ተህዋስያን ብግርነት የዳሰሳ ጥናት ፕሮግራምን አስመልክቶ ንግግር አድርገዋል፡፡
አቶ እስጢፋኖስ ጽጌ የኢንስቲትዩቱ የብሄራዊ የክሊኒካል ባክትሮሎጂ እና ማይክሎጂ ሪፈረንስ ላቦራቶሪ ቡድን መሪ የጸረ ተሕዋስያን መድሃኒት ብግርነት የዳሰሳ ጥናት የሚካሄድባቸውን ላቦራቶሪዎች ለማስፋፋት ከታቀዱት 16 ቦታዎች 9 ማቋቋም መቻሉንና ቀሪዎቹን ተግባራዊ ለማድረግ በሃገር ደረጃ የተጠናከረ የማይክሮ ባዮሎጂ ላቦራቶሪ አለመኖና በቂ የሆነ የላቦራቶሪ ግብዓት አቅርቦት አለመኖር እንዲሁም አገር አቀፍ እና አለም አቀፍ ድጋፍ ለዳሰሳ ጥናቱ ውሰን መሆኑ በታቀደው ደረጃ ማስፋፋት አለመቻሉን ይሁን እንጂ በቀጣይ ደረጃ በደረጃ ከተለያዩ አሚመለከታቸው አካላት ጋር በመቀናጀት የቅኝት የዳሰሳ ጥናት በጤና ተቋማት የሚስፋፉ መሆኑን ተናግረዋል፡፡
አቶ ገብሬ አለባቸው የፕሮግራሙ አስተባባሪ በበኩላቸው የምክክር ስብሰባው በተጠናቀቀ ወቅት በእራስ አቅም የዳሰሳ ጥናት ለማካሄድ የጤና ተቋማትን በማእከል ማጠናከር ፣ የዳሰሳ ጥናት የሚካሄድባቸውን የጤና ተቋማት ማስፋፋት እንዲሁም የቅኝት ዳሰሳ ጥናት ከሚመለከታቸው ጋር ተቀናጅቶ መሰራት እንደሚገባ ተናግረዋል፡፡ ከዚህም በተጨማሪ አስተባባሪው የመረጃ ጥራት ችግሮችን ለይቶ በማውጣት የማሻሻያ እርምጃዎችን መውሰድ፣ የማይክሮ ባዮሎጂ ላቦራቶሪ ግብዓት በዘላቂነት መፈታት እና ከተባባሪ አካላት ጋር እየተደረገ ያለው የትብብር ስራ ተጠናክሮ መቀጠል እንዳለበት በምክክር ስብሰባው ላይ የተደረሰባቸው የጋራ አቅጣጫዎች መሆናቸውን ገልጸዋል፡፡
የጤና ሚኒስቴር ተወካዮች፣ ዳሰሳ ጥናቱን የሚያካሂዱ የጤና ተቋማት ላቦራቶሪ ሃላፊዎች፣የኢንስቲትቱ የተለያዩ ዳይሬክቶሬት ባለሙያዎች እና አለማቀፍ የኢንስቲትዩቱ አጋር ድርጅት ተወካዮች በምክክር ስብሰባው ላይ እየተሳተፉ ይገኛሉ፡፡anti tewasiyana