contact us

Who's Online

We have 105 guests and no members online

colera aየጸረ ኮሌራ ክትባት ዘመቻ በምዕራብ ጉጂ ዞን አባያ ወረዳ የኢትዮጵያ የሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ምክትል ዋና ዳይሬክተር አቶ አስቻለው አባይነህ፣ የኦሮሚያ ጤና ቢሮ ምክትልና ሌሎች ሃላፊዎች እንዲሁም የወረዳው ነዋሪዎች በተገኙበት ተጀምሯል፡፡
በመክፈቻ ስነ-ስርዓቱም አቶ አስቻለው ክትባቱ በሚሰጥበት ወቅት የሕክምና ባለሙያዎች እና ተከታቢዎች ራሳቸውን እና ማሕበረሰቡን ከኮቪድ-19 በሽታ ለመከላከል የመከላከያ መንገዶችን መከተል እንዳለባቸው አሳስበዋል፡፡
ከስነ-ስርዓቱ መጨረሻም በምክትል ዋና ዳይሬክተሩ እና በክልሉ የጤና ቢሮ ምክትል ሃላፊ አቶ ደረጀ አብደና ለጋዜጠኞች መግለጫ ተሰጥቷል፡፡
የኢንስቲትዩቱ ምክትል ዋና ዳይሬክተር አቶ አስቻለው በመግለጫቸው እንደገለጹት ከ2011 ዓ.ም ጀምሮ ወረርሽኙ ከቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል በስተቀር በሁሉም ክልሎች የተከሰተ ሲሆን በተሰራው የመከላከልና የመቆጣጠር እርምጃ የኮሌራ ወረርሽኝ የተከሰተባቸው ቦታዎች ላይ 15,623 ሰዎች በበሽታው ሲያዙ 275 ሰዎች ደግሞ ሕይወታቸውን አጥተዋል፡፡ ከሐምሌ 2013 ወረርሽኙ በኦሮሚያ፣ በደቡብ ክልል 5 ዞኖች ላይ 18 ወረዳዎች፣ ሲዳማ ክልል 8 ወረዳዎችና በጋምቤላ ክልል አንድ ወረዳ ወረርሽኙ መኖሩ የሚታወቅ ሲሆን በዚህ ዓመትም ማለትም ከሐምሌ 2012 ጀምሮ በሀገራችን ኢትዮጵያ ወረርሽኙ እስከ አሁን ድረስ 2,333 የኮሌራ ኬዝ እና 44 ሞት የተከሰተ ሲሆን በአጠቃላይ ከ2011 ጀምሮ ደግሞ አስከአሁን ድረስ 17,956 ሰዎች የታመሙ ሲሆን 319 ሰዎች በኮሌራ በሽታ ሕይወታቸው አልፏል፡፡
የኢትዮጵያ የሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ከክልሎች እና ከአጋር ድርጅቶች ጋር በመተባበር የኮሌራ በሽታ ቅኝት በማከናወንና ለወረርሽኙ ፈጣን ምላሽ እየሰጠ የሚገኝ ሲሆን ባፈው ዓመት የኮሌራ ክትባት በኦሮሚያ 5 ወረዳዎች፣ በደቡብ 5 ወረዳዎች፣ በሱማሌ 3 ወረዳዎች እና በአፋር 2 ወረዳዎች እንዲሁም በአዲስ አበባ በተመረጡ ቦታዎች ላይ በ2012 የመጀመሪያ ዙር ለመጀመሪያ ጊዜ ለ 613,572 ተጋላጭ ሰዎች የኮሌራ ክትባት በተሳካ ሁኔታ በስጠት የተቻለ ሲሆን በምዕራብ ሀረርጌ ዞን አምስት ወረዳዎች ላይ ሁለተኛ ዙር 285,354 ሰዎች ክትባቱን አግኝተዋል፡፡colera b