contact us

Who's Online

We have 58 guests and no members online

hs2የኢትዮጵያ የሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት የሕብረተሰብ ጤና አደጋዎች መልሶ ማቋቋም እና የሬዚሊየንስ ዳይሬክቶሬት ከተለያዩ ባለደረርሻ አካላት ጋር በመተባበር ከጥቅምት 23 እስከ 27/2013 ዓ.ም የሚቆይ በአዳማ ከተማ በድሬ ሆቴል የሕብረተሰብ ጤና አደጋዎችን መቋቋም እና የጤና ስርዓቱን በተሻለ ሁኔታ መገንባት የሚያስችል የስልጠና ማንዋል ለማዘጋጀት አውደ ጥናት እያካሄደ ነው፡፡
የስልጠና ማንዋል ማዘጋጀት የአስፈለገበት ዋና ምክንያት ድንገተኛ የሕብረተሰብ ጤና አደጋዎችን በተሻለ መንገድ ለመቋቋም የጤና ስርዓቱን ዝግጁነት ለማጠንከር እና መሰረታዊ የጤና አገልግሎቶችን በህብረተሰብ ጤና አደጋዎች ጊዜ ለመስጠት የሚያስችል የስልጠና ማንዋል በማዘጋጀት የሕብረተሰቡን የጤና አደጋዎች ለመቆጣጠር ነው፡፡
አቶ አስቻለው አባይነህ የኢንስቲትዩቱ ም/ዋና ዳይሬክተር በአውደ ጥናቱ የመክፈቻ ስነ-ስርዓት ወቅት እንደተናገሩት የተለያዩ የሕብረተሰብ ጤና አደጋዎች በሚከሰቱ ሰዓት በቀላሉ መቆጣጠር የሚያስችል የጤና ስርዓት መገንባት አስፈለጊ ሆኖ በመገኘቱ ሁሉም የዓለም አገራት በዝግጅት ላይ ይገኛሉ፡፡ስለሆነም ሃገራችን የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝን ከመከላከልና ከመቆጣጠር አንጻር የተለያዩ ልምዶች በመውወሰድና በመጠቀም ለሃገራችን ፣ለአፍሪካ ብሎም ለዓለም ጥቅም ላይ ሊውል የሚችል ጠንካራ የጤና ስርዓት መገንባት የሚያስችል ሞጁል ማዘጋጀት ይገባናል ሲሉ ሰፊ ገለጻ አድርገዋል፡፡
ዶ/ር ያረጋል ፉፋ የሕብረተሰብ ጤና አደጋዎች መልሶ ማቋቋም እና የሬዚሊየንስ ዳይሬክቶሬት ተ/ዳይሬክተር በበኩላቸው እየተካሄድ ባለው የማንዋል ዝግጅት ላይ መሰረታዊ የጤና አገልግሎቶችን በህብረተሰብ ጤና አደጋዎች ጊዜ እንዴት መስጠት እንደሚቻል፣ ከህብረተሰብ ጤና ድንገተኛ አድጋዎች በፊት መደረግ ስላለባቸው የዝግጅት ጉዳዮች፣የህብረተሰብ ጤና አደጋዎችን የመለየት ሂደት፣በማህብረሰቡ ዘንድ ከሚከሰቱ የጤና አደጋዎች በፊት መደረግ ስላለባቸው ጥንቃቄዎች፣በህብረተሰብ አደጋ ወቅት ስለሚሰሩ ስራዎች እንዲሁም የሕብረተሰብ ጤና አደጋዎች ከተከሰቱ በኋላ ስለሚደረጉ የመከላከልና የመቆጣጠር ተግባራት በስፋት እና በጥልቀት በመፈተሸ የጤና ስርዓቱን በከፍተኛ ሁኔታ ሊያሻሽል የሚያስችል የስልጠና ማንዋል እንደሚዘጋጅ ገልጸዋል፡፡
ከጤና ሚኒስቴር፣ከተለያዩ ዩኒቨርሲቲዎች፣ከሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት እና ከተለያዩ አጋር ድርጅቶች የተውጣጡ አመራሮችና ባለሙያዎች አውደጥናቱ ላይ እየተሳተፉ ይገኛሉ፡፡hs