contact us

Who's Online

We have 347 guests and no members online

good gevernaceበኢትዮጵያ የሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት የቲቢ እና ኤች አይ ቪ ምርምር ዳይሬክቶሬት ከሪፎርምና መልካም አስተዳደር ዳይሬክቶሬት ጋር በመተባበር ከየካቲት 9 እስከ 13/2012 ዓ.ም በአዳማ ከተማ በድሬ ኢንተርናሽናል ሆቴል 19 ለሚደርሱ በኢንስቲትዩቱ በተለያዩ ኃላፊነት ቦታ ላይ ለሚሰሩ አመራሮች እና ለቅሬታ ሰሚ ኮሚቴዎች በቅሬታ አፈታት ዙሪያ ስልጠና እየተሰጠ ይገኛል፡፡
የስልጠናውን የመክፈቻ ነግግር ያደረጉት የቲቢ እና ኤች አይ ቪ ምርምር ዳይሬክቶሬት ተ/ዳይሬክተር ወ/ሮ ሳሬ አብደላ ስለስልጠናው ዓላማ ሲናገሩ በክፍል ደረጃ ቅሬታዎች ሁሌ የሚነሱና የሚኖሩ ሲሆኑ እነዚህ ቅሬታዎች ወደ ቅሬታ ሰሚ ኮሚቴ ሳይደርሱ እዚያው ክፍሉ ውስጥ ሊፈቱ ሲችሉ ወደ ቅሬታ ሰሚ ኮሚቴ እና ወደሌላ ቦታም ሲደርሱ ይታያል፤ ይህንን ችግ በተወሰነ መልኩ ለመቅረፍና ብሎም ለማስቆም ይረዳ ዘንድ የቅሬታ አፈታት ክህሎትን በሳይንሳዊ ዘዴ በማዳበር በቀጣይ የሚያጋጥሙ ችግሮችን ለመቅረፍ አጋዥ ይሆን ዘንድ ስልጠናው መዘጋጀቱን ተናግረዋል፡፡
ወ/ሮ ሳሮ ንግግራቸውን በመቀጠል የአንድ ሰው ክህሎት በአንድ ስልጠና ሙሉ ባይሆንም ጥሩ መነቃቂያ እንሚሆናቸው ገልጸዋል፡፡
የስልጠናው አስተባባሪ ወ/ሮ ትዕግስት አበራ በሪፎርምና መልካም አስተዳደር ዳይሬክቶሬት ከፍተኛ የተገልጋዮች ቅሬታና አቤቱታ ማስተናገድና መፍታት ባለሙያ ስለስልጠናው ሲናገሩ የቅሬታ ሰሚ ኮሚቴዎችን በቅሬታ አቀራረብና አፈታት ዙሪያ ሳይንሳዊ በሆነ ዘዴ ክህሎታቸውንና ግንዛቤያቸውን ከፍ ለማድረግና ወጥ የሆኑ የቅሬታ አቀራረቦችንና አፈታቶች ተግባራትን ለመፈጸም በማሰብ የተዘጋጀ ስልጠና መሆኑን የተናገሩ ሲሆን አያይዘውም ስልጠናው ከኢትዮጵያ ስራ አመራር ኢንስቲትዩት በመጡ አሰልጣኝ በጥሩ ሁኔታ እየተሰጠ መሆኑን ገልጸዋል፡፡ የስልጠናው ተሳታፊዎች ከስልጠናው በኋላ በስራቸው ለሚገኙ ሰራተኞች ከስልጠናው ያገኙትን ዕውቀት አንደሚያጋሩ ተናግረዋል፡፡
በስተመጨረሻም ወ/ሮ ትዕግስት ይህ ስልጠና እንዲዘጋጅ ከፍተኛ እገዛ ላደረጉት የቲቪ ኤች አይ ቪ ዳይሬክቶሬት ተ/ዳይሬክተርና የቅሬታ ሰሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ ለሆኑት ለወ/ሮ ሳሮ አብደላ ከፍተኛ ምስጋና አቅርበዋል፡፡good gevernace2