contact us

Who's Online

We have 355 guests and no members online

mahesen chafe1የኢትዮጵያ የሕብረተሰብ ጤና ኢንሰቲትዩት የኤቺ አይቪ ቲቢ ምርምር ዳይሬክቶሬት ከኢትዮጵያ ባዮ ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት(EBTI) ጋር በመተባበር በማህጸን በር ጫፍ ካንሰር አምጭ ተህዋስያን ( Human Papilloma Virus) ስርጭትና መጠን፣ ክትባትና የማህጸን በር ጫፍ ካንሰር ምርመራ በኢትዮጵያ በሚል ርዕስ 2ኛው አመታዊ ኮንፍረንስ በኢንስቲትዩቱ የስልጠና ማዕከል ከየካቲት 12 እስከ 13/2012 ዓ.ም እየተካሄደ ይገኛል፡፡
የኮንፍረንሱ ዋና አላማ በሽታው በሃገሪቱ ውስጥ ምን ደረጃ ላይ እንደሚገኝ እና እያደረሰ ያለውን ጉዳት በመፈተሽ በችግሩ ዙሪያ በሃገር አቀፍ ደረጃ ጥናትና ምርምር ለማድረግ እንዲሁም ለመንግስት የፖሊሲ ግብዓት ለመስጠት የተዘጋጀ ኮንፍረንስ ነው፡፡
ዶ/ር ካሳሁን ተስፋዬ የኢትዮጵያ ባዮ ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት ዋና ዳሬክተር በኮንፍረንሱ የመክፈቻ ስነ-ስርዓት ወቀት እንደገለጹት የማህጸን በር ጫፍ ካንሰር በአለም አቀፍ ደረጃ ከ530 ሺ በላይ የሚሆኑ ሴቶች በበሽታው እንደሚያዙ እና በኢትዮጵያ ደረጃ ደግሞ በዓመት ከ7000 በላይ በበሽታው እንደሚያዙ፣ከነዚህም ውስጥ ከ4000 በላይ ደግሞ እንደሚሞቱ፣ በየ3 ዓመቱ በሽታውን ለመለየት ምርመራ የሚያድርጉት ሴቶች ደግሞ 0.2 በመቶ ብቻ መሆናቸውን ተናግረዋል፡፡
አቶ ኪሩቤል እሸቱ የኢትዮጵያ የሕበረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት የኤች አይቪ ቲቢ ዳይሬክቶሬት የላቡራቶሪ አማካሪ በበኩላቸው የማህጸን በር ጫፍ ካንሰር በሽታ በግንኙነት ጊዜ የሚተላላፍና መንስኤውም Human Papilloma Virus መሆኑን፣7 0 በመቶ የሚሆኑትን ሴቶች እያጠቃ ያለው በታዳጊ ሃገር መሆኑን እና ይህንን በሽታ በሃገር ደረጃ ለመከላከል የኢትዮጵያ የሕበረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት፣የኢትዮጵያ ባዮ ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት እና የተለያዩ ዩኒቨርሲቲዎች በተገኙበት በህዳር ወር በ2011 ዓ.ም ኮንፍረንሱ መመስርቱንና አሁን አየተካሄደ ያለው 2ኛው አመታዊ ጉባኤ መሆኑን ገልጸዋል፡፡
የቫይረሱን የጉዳት መጠን፣ቫይረሱን የመለየትና ሃገር አቀፍ ደረጃ ያለው የክትባት ሁኔታ አስመልክቶ የተለያዩ ጥናቶች በኮንፍረንሱ ላይ የሚቀርቡ ሲሆን ከሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት ጋር ሰፊ ውይይት ተደርጎ በችግሩ ዙሪያ በቀጣይ መደረግ በሚገባቸው ጉዳዮች ላይ አቅጣጫ በማስቀመጥ የጋራ መግባባት ላይ ይደረሳል ተብሎ ይጠበቃል፡፡
የኢትዮጵያ የህብረተሰብ ጤና ኢንሰቲትዩት(EPHI) እና የኢትዮጵያ ባዮ ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት(EBTI) ባለሙያዎች፣ከተለያዩ ዩኒቨርሲቲዎች እና የምርምር ተቋማት እንዲሁም ከተለያዩ አጋር ድርጅቶች የተወከሉ ባለሙያዎች ኮንፈረንሱ እየተካፈሉ ይገኛሉ፡፡mahesen chafe2