contact us

Who's Online

We have 137 guests and no members online

bahel2የኢንስቲትዩቱ የባሕልና ዘመናዊ መድሐኒት ምርምር ዳይሬክቶሬት ከጤና ሚኒስቴር ጋር በመተባበር ከ25 በላይ ለሚሆኑ የባሕል መድሐኒት አዋቂዎች ዛሬ ጥር 14/2012 ስልጠና መስጠት የጀመረ ሲሆን ስልጠናውም ለ10 ተከታታይ ቀናት የሚሰጥ ይሆናል፡፡
ወ/ሮ ፍሬህይወት ተካ የባሕልና ዘመናዊ መድሐኒት ምርምር ዳይሬክቶሬት ተ/ዳይሬክተር በመክፈቻ ንግግራቸው እንደተናገሩት ስልጠናው የሚሰጠው በቅርቡ ይፋ በተደረገው የኢትዮጵያ የባሕል መድሐኒት ምርምር ፍኖተ ካርታ መሰረት አንዱ ተግባር ለባሕል መድሐኒት አዋቂዎች ስልጠና መስጠት በመሆኑ ሲሆን ይህም ስልጠና የመጀመሪያ ዙር ሲሆን ሌሎች ተከታታይ ስልጠናዎችም እንደሚኖሩ ገልጸዋል፡፡ አያይዘውም የባሕል ሕክምና ማስተባበሪያ በኢንስቲትዩቱ እንዲካተት መደረጉ ለመስኩ ማደግ ከፍተኛ አስተዋጽኦ እንደሚኖረውም አስረድተዋል፡፡
አገር በቀል መድሐኒቶችን መሰነድ፣ ከጤና ሚኒስቴር እና ከሌሎች ተያያዥ ተቋማት ጋር በጋራ ለመስራት እና በባሕል ሕክምና የሚያጋጥሙ ተግዳሮቶችን መለየት እና መፍትሔ ማስቀመጥ የሚሉት የስልጠናው ዋና ዋና አላማዎች ናቸው፡፡
ኢትዮጵያ ከ6500 በላይ የእጽዋት አይነቶች እንዳሏት ይታወቃል፡፡ በአሁኑ ወቅት የዘመናዊ ሕክምና መስፋፋት የባሕላዊ ሕክምናን ስፋት የቀነሰው ቢሆንም አሁንም ግን ከ80 በመቶ በላይ የሕብረተሰቡ ክፍል የመጀመሪያ ምርጫው የባሕል ሕክምና ነው፡፡bahel1