contact us

Who's Online

We have 215 guests and no members online

femalየኢንስቲትዩቱ የሴቶች፣ህጻናትና ወጣቶች ዳይሬክቶሬት በህይወት ክህሎት እና አደንዣዥ እጽ በወጣቱ ጤና የሚያስከትለከውን ጉዳት ግንዛቤ በማስጨበጥ ዙሪያ ለኢንስቲትዩቱ ወጣቶች ከäጉሜን 1/2011 እስከ 2/2011 ዓ.ም በደብረዘይት ከተማ በቢን ሆቴል ስልጠና ሰጠ፡፡
የስልጠናው ዋና አላማ የወጣቶች የስራ ተነሳሽነት በመጨመር በስራቸው ላይ ውጤታማ በመሆን በኢንስቲትዩቱ የሚሰጣቸውን የህብረተሰብ አገልግሎት በብቃት እንዲወጡ ለማድረግና አደንዣዥ እጽ በወጣቱ ጤና ላይ የሚያስከትለከውን ጉዳት ግንዛቤ ለማስጨበጥ የተዘጋጀ ስልጠና ነው፡፡
ስልጠናው የተዘጋጀው በሃገር አቀፍ ደረጃ 14ኛ ጊዜ ”የትምህርት ጥራትን በማሻሻል ምክንያታዊ ወጣት እንፍጠር” በሚል መሪ ቃል፤ በጤና ሚኒስቴር ደግሞ ለ3ኛ ጊዜ ”የጤናን ግብ ለማሳካት ምክንያታዊ ወጣት እንፍጠር” በሚል መሪ ቃል የተከበረውን እና በኢንስቲትዩቱ ለ2ኛ ጊዜ እየተከበረ ያለውን የወጣቶች ዓመታዊ በዓል ምክንያት በማድረግ የኢንስቲትዩቱን ወጣት ሰራተኞች ስለህይወት ክህሎትና ስለ አደንዛዥ እጽ በሰው ህይወት ላይ የሚስከትለውን ጉዳት በማስጨበጥ በኢንስቲትዩቱ የሚሰጡትን አገልግሎቶች ጥራታቸውና ተአማኒነታቸውን የተረጋገጠ ለማድረግ ታስቦ የተዘጋጀ ስልጠና መሆኑን የሴቶች ፣ህጻናት እና ወጣቶች ጉዳይ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ወ/ሮ ኑሪያ ዩሱፍ ገልጸዋል፡፡
ወጣትነት ጉልበት እና አቅም ሲሆን በምክንያታዊነት የሚመራ ወጣት መፍጠር ደግሞ ለሃገራዊ ግብ ስኬታማነት እጅግ ወሳኝ ጉዳይ ነው፡፡ስለዚህ ምክንያታዊነት ለውጤታማነትና ለተሟላ ህይወት መሰረት በመሆኑ ምክንያታዊ የሆነ ወጣት ለሃገርና ለህብረተሰቡ ብሎም ለራሱ የህይወት ጉዞ ጠቃሚ በመሆኑ ለወጣቶች የህይወት ክህሎት ስልጠና ወሳኝ ነው ሲሉ ስልጠናውን ሲሰጡ የነበሩት የስነ-ልቦና ባለሙያ አቶ ሽመልስ ገበየሁ ማብራሪያ ሰጥተዋል፡፡
ስልጠናው የልምድ ተሞክሮዎችን፣ውጤታማ እና ስኬታማ የሆኑ ሰዎችን ታሪክ በመዳሰስ በፊት ላፊት ገለጻና በቡድን ውይይት ላይ መሰረት ያደረገ የነበረ ሲሆን ስልጣኝ ወጣቶች በቀጣይ ባላቸው ክህሎትና እውቀት ጠንክረው በመስራት እራሳቸውን እና ኢንስቲትዩቱን ውጤታማ ለማድረግ የሚችሉበትን ግንዛቤ መጨበጣቸውን ከስልጠናው ሂደት መረዳት የተቻለ ሲሆን እድሜያቸው ከ18 እስከ 35 የሚሆኑ ከ60 በላይ ሴትና ወንድ ወጣቶች በስልጠናው ላይ ተሳትፈዋል፡፡femal2